በስልጠናውም የልጆች አስተዳደግ መርሆች

ሱመያ ት/ቤቶች ባሳለፍነው ዕሁድ በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ እጅግ ማራኪ የአእምሮ ስንቅ ሀገራችን በዘርፉ ካፈራቻቸው ምርጥ እንስት አሰልጣኝ አንዷ በሆነቸው ወ/ሮ መካነሰላም የተሰጠ ሲሆን በስልጠናውም የልጆች አስተዳደግ መርሆች
1.ያለ ቅድመ ሁኔታ ለልጆች ፍቅርና እምነት ማሳየት
2.ልጆች ለራሳቸው ያላቸውን ቦታና አመለካከት አዎንታዊ እንዲሆን መስራት

  1. ከልጆች ጋር በሚኖረን ግኑኝነት መደረግ ያለባቸውንና የሌለባቸው ነገሮች መለየት
  2. ጥራት ያለው ጊዜ ለልጆች መስጠት
    5.መልካም የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ማድረግና ሌሎችም ትምህርቶች በውይይትና በጫወታ እየተዋዛ ተካሂዷል፡፡ በስልጠናውም የተገኛችሁ ወላጆችም ምስጋናችንን እያቀረብን በስልጠናው ላይ ያገኛችሁትን ትምህርት ተግባራዊ ማድረጉ ስልጠናውን ፍሬማ እንዲሁም የነገውን ልጆቻችንን ይቀርጻል፡፡በቀጣይም ወላጆች በስልጠናው በእጅጉ የረካችሁና ጠቃሚ መሆኑን በገለጻችሁልን መሰረት አክስዮን ማህበሩ በቀጣይም መሰል ስልጠናዎች እንዲሰጥ የሚያመቻች መሆኑን እናረጋግጥላችኋለን፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top